የዞን አስተባባሪ ኮሚቴ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል
1.ዋና አስተዳዳሪ ሰብሳቢ
2.የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ም/ሰብሳቢ
3.ም/አስተዳዳሪ አባል
4.የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አባል
5.የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ጸሀፊ
አንቀጽ 28 የዞን ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ ተግባረና ኃላፊነት
1.ከክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት የዞኑን የፖርቲ ስራና የመንግስት ስራዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ይከታተላል፣ ይመራል
2.የፓርቲና የመንግስት ስራዎች ተቀናጅተው እንዲተገበሩ ያደርጋል፣ ይገመግማል፣ አቅጣጫ ያስቀምጣል፣
3.በዞኑም፣ ሆኑ ከዛ ውጭ የተገኙ መልካም ልምዶችን በመቀመር በዞኑ ውስጥ የማስፋት ሥራ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል፡፡
4.የሚካሄዱ የፓርቲና የመንግስት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ይከታተላል፣ ይመራል፣ እንዲሁም በዞኑ ያሉትን የፓርቲ አመራር አካላትን በቅርብ ይደግፋል፡፡
5. በየደረጃው ያሉትን የፓርቲ የመንግስት አመራር አካላትን ፖለቲካዊ ብቃት በመገንባት ተልዕኳቸውን የሚወጡ እንዲሆኑ ስራ ይሰራል፡፡
6.የፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴና ካቢኔ አባላት ምደባ የውሳኔ ሐሳብ ቀጥሎ ላለው የፓርቲ ጽ/ቤት ያቀርባሉ፣ ሲፀድቅ ያሠማራሉ፣ ለዞን ተጠሪ የሆኑ ከተሞችንና ወረዳዎችን ለክልሉ ፓርቲ ጽ/ቤት አሳውቆ ያፀድቃለል፡፡
7.ከፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴና ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የወጡ የአሰራርና የአደረጃጀት መመሪያዎች፣ የተቀመጡ አቅጣጫዎች በዞኑ በአግባቡ በስራ ላይ መዋላቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ያስፈጽማል፣ ይፈጽማል፣
8.በዞኑ የአመራር፣ የሕዝብና የተፎካካሪ ፓርቲ ሁኔታን በዝርዝር በማወቅ እየገመገመ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል፡፡
9.ተጠሪነቱ ለክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ይሆናል፡
አንቀጽ 29 የዞን ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ አሰራር
1.በወር አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል፣ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ከዚያም ባጠረ ጊዜ ሊያካሄድ ይችላል፡፡
2.ምልዓተ ጉባኤው 50+1 ነው
3.ውሳኔዎች በተባበረ ድምጽ የሚፀድቁ ሆኖ ድምጽ መስጠት አስፈላጊ ሲሆን በ50+1 የተደገፈ ሀሳብ የኮሚቴው ውሳኔ ሆኖ ይፀድቃል፡፡ እኩል ድምጽ ከመጣ ሰብሳቢው የደገፈው ሀሳብ ፀዳቂ ይሆናል፡፡
1. የፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ሰብሳቢ
2. የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ም/ሰብሳቢ
3. የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አባል
4. የሲቪክ ተቋማትና ፖለቲካ ፓርዎች ዘርፍ ኃላፊ አባል
5. የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ፀሀፊ
6. የወጣቶችና ሴቶች ሊግ ሰብሳቢዎች አባል
7. የፓርቲው ጽ/ቤት ኃላፊ እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች የስራ ኃላፊዎችን ሊጨምር ይችላል፡፡
አንቀጽ 31 የዞን ፓርቲ ጽ/ቤት አመራር ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊት
1.የፓርቲው ጽ/ቤት በመተዳደሪያ ደንብ ላይ በተቀመጠው ተልዕኮ መሰረት የዞን የፖለቲካ፣ የአደረጃጀትና የሕዝብ ግንኙነት ስራ ማዕከል ሆኖ ያገለግላል፡፡
2.የፓርቲና የርዕዮተ ስርፅት ተግባርን በየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ተመስርቶ ያቅዳል ይተግብራል በአባላት ግንባታና ግብረመልስ ላይ አትኩሮ ይሰራል፡፡
3.ከክልሉ ፓርቲ ጽ/ቤት የሚወርዱ ዕቅዶችን መነሻ በማድረግ ከራሱ የዞን ሁኔታ ጋር በማጣጣም የፖለቲካና የአደረጃጀት ስራዎችን ያቅዳል፣ ፈፃሚውን አካል ኦረንቴሽን ሰጥቶ ያሰማራል፡፡ የስራውንም አፈፃፀም ይከታተላል ይመራል፡፡
4.በየደረጃው ያለው ፓርቲ አደረጃጀት አመራርና አባላት በስራቸው ግምባር ቀደም እንዲሆኑ ፖለቲካዊ ግንዛቤያቸውን እንዲዳብር ያደርጋል፡፡
5.የአባላት የዕለት ተዕለት ግንባታ ስራን በተቀመጠው አቅጣጫ እተከናወነ መሆኑንና በየወቅቱ ያለውን የአባላት ፖለቲካዊ ሁኔታ በመገምገም የግንባታ ስራው እያጠናከረ ይሄዳል፡፡ ጠንካራ የህዋስና መሰረታዊ ድርጅት አመራር የመፍጠር ስራን ያቅዳል፣ ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፣ ይመራል፡፡
6.በዞኑ፣ የሚካሄደውን የአባላትና የአመራር ስልጠና፣ ሴሚናር የመ/ድርጅቶች ኮንፈረንስ ያስተባብራል፣ ይመራል፡፡
7.የፓርቲው የአሰራርና የአደረጃጀት መመሪያዎች፣ የማዕከላዊ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ ውሳኔዎችና አቅጣጫዎች በዞኑ በስራ መተርጐማቸውን ይከታተላል ያስፈጽማል፡፡
8.በዞኑ፣ ውስጥ በሚገኙ የአባላት ማህደር፣ መረጃ፣ የፓርቲ ሰነዶችና የፓርቲውን ገንዘብና ንብረት በበላይነት ያስተዳድራል፣ በጥንቃቄ እንዲያዙና በአግባቡ ሥራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፡፡
9.የዞኑ የአመራር፣ የአባላት፣ የሕዝብና የተፎካካሪ ኃይሎች ሁኔታን በየጊዜው እየተከታተለ ተገቢው የማስተካከያ አቅጣጫ ሰጠ ይሄዳል፡፡ የአመራርን ስነ-ምግባርና የመፈፀም ብቃት በማዳበር የአባሉን የተደራጀ አሀዳዊ እንቅስቃሴ የሚመራ ጠንካራ አመራር ስራ ይደግፋል፣ ብቃት ያለው አመራር በበቂ ቁጥር እንዲፈጠሩ አቅዶ ይሰራል፣
10.የአመራሩን ስነ-ምግባርና የመፈጸም ብቃት በማዳበር የአባሉን የተደራጀ አሃዳዊ እንቅስቃሴ የሚመራ ጠንካራ አመራር በበቂ ቁጥር እንዲፈጠር አቅዶ ይሠራል፡፡
11.በልሳናትና በራሪ ጽሑፎች እንዲሁም በብልጽግና መጽሔት ላይ ለሚካሄደው የአባላት ግንባታ ከክልል ፓርቲ ጽ/ቤት የሚተላለፉትን መልዕክቶች በብቃት ለማስረጽ በሚያስችል አግባብ ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡
12. በሁለት ሳምንት ከክልሉ ፓርቲ ጽ/ቤት ጋር የመረጃ ልውውጥ ያደደርጋል፣ በወር አጭር የጽሑፍ ሪፖርት፣ በየ3 ወሩ አጠቃላይ የስራ ሪፖርትና የጋራ መድረክ ይኖረዋል፡፡ በየስድስት ወሩ የግምገማ እና ሂስ ግለሂስ ተደርጐ ማህደር ይሞላል፡፡
13. ተጠሪነቱ ለዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴና ለክልሉ ፓርቲ ጽ/ቤት አመራር ኮሚቴ ይሆናል፡፡
አንቀጽ 33 ፖለቲካ ዘርፍ
1.በአባላት ግንባታና በፖለቲካና ርዕዮተ አለም ስርጸት ላይ አተኩሮ ይሰራል፡
2.በተዘጋጁ ሰነዶች ላይ በመመስረት ለውይይትና ለስልጠና የሚያግዙ ጭብጦች ድምዳሜ ሊደረስባቸው የሚገቡ አንኳር ጉዳዮችን ለይቶ ያዘጋጃል፣
3.የአመራርና አባላትን አቅም መገንባት የሚያስችሉ ልሳናት እና የንድፈ ሃሳብ ጽሁፍ በተመረጡ ርዕሶች ላይ ጊዜያቸውን ጠብቀው በጥራት እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤ ያዘጋጃል፣
4.ወቅታዊ፣ከየመድረኩ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የሚዛመዱእና የጋራ አመለካከት ለመፍጠር የሚያግዙ መልዕክቶችንና አጀንዳዎችን በመቅረፅ አስራርና አባላት የተሟላ ግልፅነት እንዲኖራቸው ያደርጋል፣
5.ከተግባር ጋር በጥብቅ የተቆራኘ የዕለት ተዕለት የፖለቲካ የአቅም ግንባታ ስራን ያቅዳል፤ ያስፈጽማል፤
6.የፖለቲካ ስራን ያቅዳል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፣ ሪፖርት ያቀርባል፤
7.በፖለቲካ እና ርዕዮተ ዓለም ስርፀት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት ለቀጣይ ጥናትና ምርምር ግብዓት የሚሆን ግብረ-መልስ ያዘጋጃል፣ለጥናትና ምርምር ይሰጣል፡፡
8.ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚኖረንን የግንኙነት ስራ ከጽ/ቤቱ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት ተከታትሎ መፈፀምና የፓርቲዎችን ሁኔታ ግምገማ በየጊዜው በመለየትና በመያዝ ለፖለቲካ ስራ በግብአትነት ጥቅም ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣
9.በዞን ደረጃ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ ብልፅግናን ወክሎ በመወያየት እና በመመካከር በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ይነድፋል፤ ተግባራዊ ይደርጋል፣
10.ከዞን ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት ጋር ያለንን ህጋዊና ተቋማዊ የስራ ግንኙነት ጽ/ቤቱን በመወከል ያስተባብራል፤ ይመራል፡፡
አንቀጽ 34. የአደረጃጃት ዘርፍ
1.በሁሉም የአደረጃጀት ደረጃዎች/ህዋሳት፤መሰረታዊ ድርጅቶች…./ በተግባር ግንባር ቀደምና አርአያ የሆኑ አባላት እንዲመለመሉ የማድረግ ስራ ተሟልቶ መተግበሩን ያረጋግጣል፡፡
2.የብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት የሆኑ ህዋሳት፤ መሰረታዊ ድርጅቶችን፤ ወረዳዎችን ያደራጃል፤ ሁሉም አባላት በህዋስና መሰረታዊ ድርጅቶች መደራጀታቸውን ያረጋግጣል፣
3.አባላትና አመራሮች ለተለያዩ ሃላፊነቶች የሚደረጉ ምልመላዎች፣ ምደባዎችእና ሹመቶች እንዲሁም የስራ ስምሪቶች በድርጅቱ የአሰራር መመሪያ መሰረት እንዲከናወኑ ያደርጋል፣
4.ለስልጠናእና ለሌሎች የአቅም ግንባታ ተግባራት የሚመለመሉ አባላትና አመራሮች ግልጽ መስፈርት በማዘጋጀት እንዲከናወን ያደርጋል፤
5.የአባላት እና አመራር ማህደሮችና የተለያዩ የድርጅት ሰነዶች በአግባቡ በማደራጀት እንዲያዙ ያደርጋል፡፡ ይህም የሚመራበት አስራርና መመሪያ እንዲኖር ያደርጋል፤
6.የአባላትና አመራር መረጃ ስርዓት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ (ዲጂታላይዜሽን) የተደገፈ እንዲሆን ያደርጋል፤
7.የፓርቲውን መሰረታዊ ሰነዶች የድምጽ፤የምስልና የጽሁፍ (ሃርድእናሶፍትኮፒ) በጥንቃቄና በዘመናዊ መንገድ እንዲያዙ ያደርጋል፤ ጉባኤ ሪፖርቶችንና ቃለጉባኤዎች በአግባቡ እንዲያዙ ያደርጋል፤ በየዓመቱ ስራ ላይ የዋሉ እቅዶች፤ ግምገማዎች፤ ከተለያዩ አካላት ጋር የተደረጉ ግንኙነቶች ከየዘርፉ ተሰባስበው በሰነድነት እንዲያዙ ያደርጋል፤ የቤተ- መጽሁፍት አገልግሎት ይሰጣል፤
8.በየጊዜው በሚካሄድ ክትትል ላይ ተመስርቶ በየደረጃው ላለ የአመራር እርከን የሚሆን የአመራር ፑል ያዘጋጃል፤
9.በየደረጃው በሚገኙ አደረጃጀቶች ወቅታዊ ግምገማ መካሄዱን እንዲሁም ለአመራርና ለአባላት በየወቅቱ ደረጃ የማውጣት ስራ በመስራት ጠንካራ አፈፃፀም ያላቸዉ አመራርና አባላት የሚበረታቱበት ስርዓት እንዲመሰረት ያደርጋል፤
10.የአሰራርእና አደረጃጀት መመሪያዎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፤ በሁሉም ደረጃ በአባላትና አመራር አካላት ታወቀውና ታምኖባቸዉ በተሟላ መልኩ ተግባር ላይ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤
11.የፓርቲውን አሰራርንና ደንብን የሚጥሱ አባላትእና የአመራር አካላት በድርጅት ህግና ደንብ መሰረት ተገቢው የእርምት እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑን ያረጋግጣል፤ የእርምት እርምጃዎችን ይወስዳል፤
12.የሴቶችና ወጣቶች ሊጎች በአደረጃጀትና አሰራር መመሪያ መሰረት መደራጀታቸውን ያረጋግጣል፣ ከአደረጃጀት አኳያም ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
13.በሲቪክ፣ የሙያና የብዙሃን ማህበራት፣ ፌዴሬሽኖች፣ ፎረሞች፣ ሌሎች
የምሁራንና የባለሃብት አደረጃጀቶችን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፤ ይደግፋል፡፡
14.በተግባር ሂደት የተገኙ ምርጥ ልምዶች በመቀመርእና በማደራጀት አደረጃጀቶች ያሉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ግበረ መልስ ይሰጣል፤
15.የአደረጃጀት ስራን ያቅዳል፣ይመራል፤ይገመግማል፤ሪፖርት ያደርጋል፡፡
አንቀጽ 35 የሲቪክ ተቋማትና ፖለቲካ ፓርቲዎች ዘርፍ
1.የሴችና የወጣቶች ሊጐችን አደረጃጀቶችን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፤ ይደግፋል፣
2.በሲቪክ፣ የሙያና የብዙሃን ማህበራት፣ ፌዴሬሽኖች፣ ፎረሞች፣ ሌሎች የምሁራንና የባለሃብት አደረጃጀቶችን ያስተባብራል፣ ይከታተላል፤ ይደግፋል፣
3.ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚኖረንን የግንኙነት ስራ ከጽ/ቤቱ በሚሰጠው አቅጣጫ መሰረት ተከታትሎ መፈፀምና የፓርቲዎችን ሁኔታ ግምገማ በየጊዜው በመለየትና በመያዝ ለፖለቲካ ስራ በግብአትነት ጥቅም ላይ እንዲዉል ያደርጋል፣
4.በየጊዜው የሚካሄዱ አካባቢያዊ ምርጫዎችን በአሸናፊነት ለመወጣት የሚያግዝ የምርጫ ስትራቴጂ፣ እቅድ ያዘጋጃል፣ የተግባር አፈፃፀሙንም ይመራል፣
5.በዞን ደረጃ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ መድረክ ብልጽግናን ወክሎ በመወያየት እና በመመካከር በዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሂደት ውስጥ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ይነድፋል፤ ተግባራዊ ይደርጋል፣
6.ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በዞን ደረጃ በሚያደርጉት ክርክርና ውይይት ድጋፍ ያደርጋል፤
7.ከአካባቢው ምርጫ ቦርድ ፅ/ቤት ጋር ያለውን ህጋዊና ተቋማዊ የስራ ግንኙነት ጽ/ቤቱን በመወከል ያስተባብራል፤ ይመራል፣
8.የስራ ክፍሉን ስራዎች ያቅዳል፣ ይመራል፤ ይገመግማል፤ ሪፖርት ያደርጋል እንዲሁም ሌሎች ወቅታዊ ተግባራትን ይመራል፡፡
9.የፓርቲን የፖለቲካና ድርጅት ስራዎችን በተለያዩ ዘዴዎች በቀጣይነት የማስተዋወቅ ስራ ይሰራል፣
10.ከተለያዩ የሚዲያ አካላት ጋር በመተባበር ስለፓርቲያችን ወቅታዊ መረጃዎችን ይሰጣል፣
11. የህዝቡን ሁለንተናዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ይዘግባል፣ የህዝቡን ወቅታዊ ፍላጎት በዳሰሳ መለየትና በተለዩት ጉዳዮች ላይ የፓርቲውንን አቋም በተለያዩ ዘዴዎች ያሰራጫል፤
12.ተጠሪነቱ ለጽ/ቤት ሃላፊ ይሆናል
አንቀፅ 36 የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ
1.የጽ/ቤቱ የገንዘብ፣ የሰዉ ሀብትእና ንብረት አስተዳደር ስራዎች ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራርን የሚከተልበትን ሥርዓት ይዘረጋል፤
2.ጽ/በቱን የበጀት ጥያቄ ይተነትናል፣ ማናቸውንም ወጪ በተፈቀደው የበጀት መመሪያ መሰረት እንዲፈፀም ያደርጋል፤
3.የሰዉ ሀብት አስተዳደር በዘመናዊ አግባብ የማደራጅትና የመምራት ተግባራትን
አግኙን